ስፖርት

ሰበር ዜና

ኢትዮ ኖርዌይ የስፖርት ቡድን ኣንደኛ ዲቪዚዮን በኣውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ከጁላይ 26 እስከ 30 2016 ኔዘርላንድስ ሄግ ላይ የተዘጋጀውን ውድ ድር ዋንጫ ወሰደ:: በተያያዘ ዜና ኢትዮ ስዊደን የሁለተኛ ዲቪዚዮንን ዋንጫ ወስዷል::የዋንጫ ሽልማቱን ስነስርዓት ይከታተሉ::ኢትዮ ኖርዌይ ዋንጫ የወሰደው ኢትዮ ስዊዝን በማሸነፍ ነው:: የዋንጫው ጨዋታ ፊልም በቅርብ ይለቀቃል::

የኢትዮ ኖርዌይ ስፖርት ቡድን 1 በኣውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ከጁላይ 25 እስከ 30 2016 ኔዘርላንድስ ሄግ ላይ በሚካሄደው የስፖርት ውድድር ለዋንጫ ማለፉን ኣረጋገጠ:: ቡድኑ ለዋንጫ ማለፉን ያረጋገጠው ኣዘጋጁን ኣኢትዮ ሆላንድን 2ለ0 በማሸነፍ ነው:: በኢትዮ ኖርዌይና በኢትዮ ሆላንድ የእግር ኳስ ቡድን መካከል የተካሀደውን ጨዋታ በከፊል ይመልከቱ::

በኣውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ከጁላይ 25 እስከ 30 2016 ኔዘርላንድስ ሄግ የባህል ምሽት 29-07-2016

ኢትዮ ኖርዌይ ከኢትዮ ኮለንና ኢትዮ ናይል ለንደን ጋር ያደረገውን ጨዋታ ይመልከቱ 29-07-2016

የኢትዮ ኖርዌይ ስፖርት ቡድን 1 በኣውሮፓ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ከጁላይ 25 እስከ 30 2016 ኔዘርላንድስ ሄግ ላይ በሚካሄደው የስፖርት ውድድር ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፉን ኣረጋገጠ:: ቡድኑ ወደ ሩብ ፍጻሜ ማለፉን ያረጋገጠው ዛሬ ጁላይ 29-2016 ኢትዮ ፍራንክፈርትን 2 ለ 0 በማሽነፍ ነው:: ጁላይ 28-2016 ኢትዮ ናይል ለንደንን 1 ለ 0 ኢትዮ ኮለንን 2 ለ 0 ኣሸንፏል:: በተያያዘ ዜና ኢትዮ ኖርዌይ ቡድን 2 ኢትዮ ኦስትርያን 2 ለ 0 ጁላይ 28-2016 ኣሽንፏል:: ቡድኑ ባሳየው ጨዋታ ከተመልካቹ ከፍተኛ ድጋፍ ኣግኝቷል::

ኢትዮ ኖርዌይ የስፐርት ቡድን በኔዘርላንድስ ለሚካሄደው ለ2016 የኢትዮ ኢሮፕ የእግር ኳስ ውድድር ያደረገው ዝግጅት ምን ይመስላል?

ከቡድኑ አሰልጣኝ አቶ አሳየኸኝ ጥላሁን ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ

05-07-2016, Oslo ,Norway

የኣስራ ሶስተኛ የኢትዮ-ኢሮፕ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ የክቡር እንግዳ ከነበሩት ኣስልጣኝ ስዩም ኣባተ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ:: ኢትዮጵያዊያን ልዩ የእግር ኳስ ጨዋታ ችሎታ ኣላቸው ይህንን ችሎታችንን በማውጣት ኣገራችንን ከታላላቅ ኣገሮች ጎን ለማሰለፍ ዲያስፖራው ትልቅ ሐብት ነው:: ኢትዮ-ኖርዌይ ቡድን ትልቅ ኣቅም ያለውና ተስፍ ሰጭ ነው:: የሚሉትንና ሌሎች ጠቃሚ መልዕክቶችን ኣስተላልፈዋል:: ስፖርትና ባህል ኣገራችንን ማንነታችንን ከማንስተዋውቅበት ኣንዱና ቁልፉ ዘዴ ነው
ኢትዮ ኖርዌይ ቲቪ በኖርውዌይና በሌሎች ኣገሮች የሚኖሩ ወጣቶች የስፖርት ችሎታቸውን እንዲያዳበሩ በሚደረገው ጥረት ማበረታታቱን ይቀጥላል::

ኣቶ ኣሳየኸኝ ጥላሁን የኢትዮ ኖርዌይ የእግር ኳስ ቡድን ኣስልጣኝ እና ከኣቶ ዳንኤል እሽቴ የኢትዮ ለንደን የእግር ኳስ ቡድን ኣስልጣኝ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
የኣስራ ሶስተኛው ኢትዮ ኢሮፕ የስፖርትና ባህል ፌስቲቫልን ኣስመልክቶ የተደረገ ቃለ ምልልስ::
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካፕቴን ኣዳነ በሚቀጥለው ለኢትዮ ኖርውዌይ ለመጫወት መጠየቁና ሌሎች መረጃዎችን ኣካቷል በመጨረሻው ታዳሚው ህዝብ ጉራጌኛ ሲጨፍር ተካቷል
ከኣስልጣኝ ስዩም ኣባተ ጋር የተደረገው ጥያቄና መልስ በቅርብ ቀን ይለቀቃል

መላካም
ETNK
Frankfurt,

18-07-2015
Ethio Europe Sport 13 th compitaiton/Frankfurt-2015 Opening Cermony.
14-18/2015

በፍራክ ፈርት ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የኣውሮፓ የእግር ኳስ ውዽ ድር ኢትዮ ኖርዌይ ኣንደኛ ዲቪዚዮን
ከምድቡ እየመራ ነው:: ወደ ሩብ ፍፃሜ ለማልፍ የሚጠበቅበት ንድ ኣነጥብ ብቻ ነው
በኣሁኑ ሰዓት ከኢትዮ ለንደን ጋር እየተጫወተ ነው::
ውድድሩ ጭፍራው ገበያው ሁሉ ነገር ደርቷል ሞቅ ደመቅ ያለ ነው ኢትዮጵያውነት መንፍስ ኣየሩን ሞልቶታል::
ኢትዮ-ኖርዌይ ቡድን ከኢትዮ ሙኒክ ጋር ያደረገውን ውድድር ይመልከቱ የቡድኑን ኣሰልጣኝና ሃላፊ የኣቶ ኣሳየኸኝ ጥላሁንን ኣስተያየት ያድምጡ::
16-07-2015
13:00

ETNK, Frankfurt

ኢትዮ ኖርዌይ ከ ኢትዮ ስዊዝ ጋር ያደረገው ጨዋታ ኢትዮ ኢሮፕ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል
ፍራክፈርት, 17-07-2017, Frankfurt Germeny

የኢትዮ ኖርዌይ የእግር ኳስ ቡድን ከቱርክ ኖርዌይ ጋር ያደረገው ውድድር ሙሉ ጨዋታ
የቡድኑ ኣሰልጣኝና መሪ ከኣቶ ኣሳየኸኝ ጥላሁን ጋርና በእለቱ ግብ ካስቆጠሩ ተጫዎቾች ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ::
Leave a Reply

Your email address will not be published.