Ethiopian Community in Norway majior activities 2013

ሰበር ዜና

የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኖርወይ ከ17 ዓመታት በላይ በ ኦስሎና ኦስሎ ዙሪያ በማተኮር ከፍተኛ ሰራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በሁሉም የኖርወይ ክፍል ለሚገኙት ወደ 7000 የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን በማህበሩ የመታቀፍ እድል ለመፍጠር 12 ቅርንጫፎችን እየከፈተ መሆኑን ኣስታወቀ::የቅርነጫፍ ማህበርነቱን ፎርማሊቲ በተቀላጠፈ መንገድ በማከናወን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኖርወይ ቲንግቮል ቅርንጫፍ የበኩር ልጅ ሆኖ ተመዝግቧል። ለስራው መፋጠን ከፍተኛ ኣስተዋፅዖ ያበረከቱት የቅርንጫፉ ምክትል ሊቀመንበር ወጣት እምሻው ጫኔ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኖርወይ ኢማኖ ዋናው መስሪያ ቤት ማዕከል በኦስሎ ከተማ ለመግዛት ከፍተኛ ልምድና ፍላጎት ያላቸውን 6 አባላት ያሉት ኮሚቴ በማወቀር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑ ታውቋል። የቤት ኣፈላላጊ ኮሚቴውም ያከናወናቸውንና ሊሰራቸው ያሰባቸውን ስራዎቸ በግልጽ ከኣባላት ፊት ቀርቦ ኣስርድቷል። ይህ እንቅስቃሴ የማህበሩን ኣባልት በከፍተኛ ሁኔታ ኣነቃቅቷል። በስፍራው የተገኙት የተለያዩ ድርጅቶችና የሃይማኖት መሪዎችም ስራውን በከፍተኛ ሁኔታ የደገፉት ሲሆን ትንሿ ኢትዮጵያችንን በኖርወይ ሊለ ኢትዮጵያ ኢ ኖርጌ በጋራ ማጣናከር ለእኛም ሆነ ለልጆቻችን የኣይዴንቲቲችን ወይም የማንነታችን ምልክት ስለሆን ምርጫ ሳይሆን ግድይታቻን ነው ብለዋል።

ማህበሩ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በኖርወይ አገር ኗሪ የነበሩ በሰው ሰራሽ አደጋ ህወታቸውን ያጡትን ሁለት ኢትዮጵያዊን ሴቶች ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር የ ኢትዮጵያን ባህል በተከተለ መንገድ የሀዘን ሰነስርዓት ያስፈፀመ ሲሀኖነ ችገሩን ከስሩ ለመቅረፍ በቤተሰብ ወዝግብ ወይም ግጭት ዙሪያ ሁለት ሴሚናሮችን ሰጥቷል ወደ ፊትም በሰፊው አጠናከሮ እንደሚቀጥል ተብራርቷል። ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያዊያንን ሰባዊ መብት ለማሰከበርና አጋዥነቱን ለማሳየት ሰላማዊ ሰለፎችን አዘጋጅቷል ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተሳተፏል። እንዲሁመ ለማህበሩ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ላበረከቱ 2 አባልትና በየኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኖርወይ የሴቶች ክፍል ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላደረጉ 4 ሴቶች የምስክር ወርቀት ማበረከቱን በ23.11.2013 ባደረገው አጠቃላይ አመታዊ ስብሰባ ላያ ተብራርቷል።
በማህበሩ ሊቀመንበር በአቶ ፋሲል አለባቸው የቀረበውን ዝርዝር ሪፖርት ወደፊት እናቀርባለን።

ኢቲንኮ